ኢትዮጵያ በኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ብቻ 146 ሚሊየን ዶላር ማጣቷ ተነገረ
ቶፕ 10 ቪፒኤን የቴክኖሎጂ ኩባንያ እንዳስታወቀው፣ በትግራይ ክልል የነበረውን ጦርነት ተከትሎ ለአንድ አመት ሙሉ የኢንተርኔት አገልግሎት በመዘጋቱ ሃገሪቱ 146 ሚሊዮን ዶላር ማጣቷን አስታውቋል።
አሁንም ቢሆንም በመላው ሀገሪቱ ኢንተርኔት በመቋረጡ ሚሊዮን ዶላሮችን እያጣች ትገኛለች ብሏል።
ኢንተርኔት ከተዘጋ ዛሬ 28ኛ ቀኑን የያዙ ሲሆን መንግሥት እስካሁን ስለጉዳዩ ያለው ነገር የለም።
መንግሥት የዘጋውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲከፍት የተሉያዩ አካላት ግፊት በማድረግ ላይ ሲሆኑ የኢትዮጵያ ሚዲያ ምክር ቤት እና ኢሰመኮ ከሰሞኑ ኢንተርኔት እንዲለቀቅ ከጠየቁ ተቋማት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።
ኢትዮጵያ በዓለም ላይ የኢንተርኔት አገልግሎት እቀባ ከሚፈጽሙ ሀገራት መካከል አንዷ እንደሆነች ኔትብሎክስ ከዚህ በፊት ባወጣው ሪፖርት ገልጿል።
ቲክቶክ፣ዩቲዩብ፣ቴሌግራም እና ፌስቡክ በኢትዮጵያ ጉደብ የተደረገባቸው የማህበራዊ ትስስር ገጾች ናቸው።