በአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ሁለት ”የጦር ጄቶች እጅግ ዝቅ ብለዉ በረሩ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እኩለ ቀን 6 ሰዓት አካባቢ ” ሁለት ተዋጊ የጦር ጄቶች ” ዝቅ ብለው መብረራቸውን አሻም ተመልክታለች፡፡

አሻም ጉዳዩን ለማጣራት የመከላከያ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነን አነጋግራለች፡፡
ኮሎኔል ጌትነት ” የጦር ጄቶች ዝቅ ብለው መብረራቸውን ” አረጋግጠው፣ ” የጦር ጄቶቹ ዝቅ ብለው የበረሩት ልምምድ እየተደረገ ስለሆነ” ነው ብለዋል፡፡

”በመጪው የአድዋ ድል በዓል ደግሞ የጦር ጄቶች በስፋት ትዕይንት እንደሚያሳዩ”ም ተገልጿል፡፡

የጦር ልምምዱ እስካሁን የተደረገው ብቻ ነው ወይስ ቀኑን ሙሉ ይቀጥላል” ስትል ላነሳችላቸው ጥያቄ ” ይህ ምስጢር ነው፤ ነገር ግን ሁሉም ሰላም ነው፡፡” ሲሉ መልሰዋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *