ምስሎቹ ኢትዮጵያ የታጠቀቻቸውን C-130 ሄርኩሊዝ የጦር አውሮፕላኖችን ያሳያል?

አንድ የፌስቡክ ፖስት ግንቦት 7 ፤ 2014 ዓ.ም ኢትዮጵያ የታጠቀቻቸው C-130 ሄርኩሊዝ ጀቶች የሚል ፅሁፍን አያይዞ አምስት ምስሎችን አጋርቶ ነበር።

ይህ የፌስቡክ ፖስትም ከ44 ጊዜ በላይ ሲጋራ ከ500 በላይ ግብረ መልሶችንም ማግኘት ችሎ ነበር።

ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ምስሉን አጣርቶ መረጃውን በከፊል ሀሰት ብሎታል። 

በህወሓት እና በፌደራል መንግስቱ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት እስካሁን ድረስ ያልተፈታ ችግር ሆኗል። 

ከጥቂት ወራት በፊት ለሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት በሚል በፌደራሉ መንግስት የቀረበውን የተኩስ አቁም ስምምነት በህወሓት ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቶ የነበረ ሲሆን ይህ ስምምነት ለሰላም ንግግር እና ግጭቱን ለማቆም ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ተገምቶ ነበር። 

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከታወጀ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና በህወሓት አመራር በሆኑት ደብረፅዮን ገብረሚካኤል መካከል የቀጥታ የስልክ ንግግር (ውይይት) ተደርጓል የሚሉ ያልተረጋገጡ ሪፖርቶች ሲወጡ ነበር።

በዩትዩብ በተለቀቀ አንድ የድምፅ መረጃ መሰረት የህወሓት ከፍተኛ የጦር አመራር የሆኑ አንድ ሰው ከታደሰ ወረደ ጋር በመሆን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም የሆኑት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን በሞሪሽየስ አግኝተው እንዳወሯቸው ገልፀዋል። 

ነገር ግን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከህወሓት አመራሮች ጋር ተገናኝተው ስለ መወያየታቸው የሚሰራጨውን መረጃ ሀሰት እና መሰረተ ቢስ መሆኑን ተናግረዋል።

ህወሓት በመግለጫዎቹ ግጭቱን ለማቆም ሰላማዊው መንገድ የማይሳካ ከሆነ በጦርነቱ እንደሚቀጥል ገልጿል

ህወሓት በተለያዩ ጊዜያቶች የፌደራል መንግስቱ እና የክልል ባለስልጣናት እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል እንዳይገባ እየከለከሉ ነው በሚል በተደጋጋሚ የተለያየ ክስ ሲያቀርብ የቆየ ሲሆን አሁንም ወደ ትግራይ ክልል የደረሰው እርዳታ በቂ አለመሆኑን ተናግሯል።

ከሳምንታት በፊትም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን በሁመራ በአካል ተገኝተው ጎብኝተዋል። 

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአንፃሩ ህወሓት በተለያዩ የትግራይ ከተሞች የህዝብ ለህዝብ ውይይት አካሂዶ የነበረ ሲሆን የህወሓት አመራር የሆኑት ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ፤ ፈትለወርቅ ዘውዴ ፤ ጌታቸው ረዳ እና አለም ገብረዋህድ ተገኝተው ውይይቱን መርተውታል።

ግንቦት 2 ቀን 2014 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ የህዝብ ውይይት ደብረጽዮን ገብረሚካኤል “ለሰላም ያደረገነው ጥረት ስላልተሳካ አሁን ለመጨረሻው የጦርነት ምዕራፍ እንድትዘጋጁ” በማለት ለህዝቡ ጥሪ አቅርበዋል።

በቅርቡ አዳዲስ የወረራ እና የግጭት ሪፖርቶች እየወጡ የሚገኙ ሲሆን ይህም ሁኔታ ሀገሪቷ በድጋሚ ሙሉ በሙሉ ወደ ጦርነት እንዳትገባ ስጋትን ፈጥሯል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም ህወሓት የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ ነው በማለት ህወሓት ወደሌላ ጦርነት እንዳይገባ  የአውሮፓ ህብረት ጫና እንዲያደርግበት የፈደራሉ መንግስት ጠይቋል።  

ይህ የፌስቡክ ፖስትም ኢትዮጵያ ያሏትን የC-130 ሄርኩሊዝ አውሮፕላን ጀቶችን ያሳያል በማለት አምስት ምስሎችን አጋርቷል። 

የአሜሪካ መንግስት ግንቦት 29 ፤ 2010 ዓ.ም ላይ C-130 ሄርኩለስ የጦር አውሮፕላኖችን ሀገሪቱ ለምታካሄደው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ እንዲያግዛት ለኢትዮጵያ አስረክቧል። 

የፌስቡክ ፖስቱ ከተጠቀመባቸው ምስሎች መካከል አንዱ ይህ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የለገሰችው የጦር አውሮፕላን ይገኝበታል። ይሁን እንጂ ከአምስቱ ምስሎች ቀሪዎቹ አራቱ የተወሰዱት ከሌላ እትሞች ሲሆን ኢትዮጵያ የታጠቀችውን C-130 ሄርኩለስ የጦር አውሮፕላኖችን አያሳዩም።   

By New admin

10 thoughts on “ምስሎቹ ኢትዮጵያ የታጠቀቻቸውን C-130 ሄርኩሊዝ የጦር አውሮፕላኖችን ያሳያል?

  • The VOCAL 100 club is our monthly lottery which raises money for carer support and pays out half of the fund in cash prizes. This

  • The best dubs go beyond the basics of the format, and make those vocal77 loops sound as if they absolutely need to be vocal77 repeated.

  • The best dubs go beyond the basics of the format, and make those vocal77 loops sound as if they absolutely need to be vocal77 repeated.

  • The best dubs go beyond the basics of the format, and make those vocal77 loops sound as if they absolutely need to be vocal77 repeated.

  • Wow Thanks for this thread i find it hard to see very good information and facts out there when it comes to this blog posts appreciate for the information website

  • Wow Thanks for this site i find it hard to search for smart resources out there when it comes to this subject matter thank for the blog post site

  • Wow Thanks for this post i find it hard to realize awesome information and facts out there when it comes to this content appreciate for the content site

  • Wow Thanks for this page i find it hard to come across awesome data out there when it comes to this material appreciate for the blog post website

  • Wow Thanks for this thread i find it hard to come across excellent tips out there when it comes to this material thank for the post website

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *